Aman Nesh Woy

Aman Nesh Woy

Ephrem Tamiru

Длительность: 7:35
Год: 1990
Скачать MP3

Текст песни

ፍቅሬ ያለሽበት አገር አማን ነው ዎይ
አገር አማን ነው ዎይ
አንቺስ ሰላም ነሽ ዎይ
ሰሞኑን አማን ነሽ ዎይ
አገር አማን ነው ዎይ
ይጨንቀኛል ዝም ብሎ ይጨንቀኛል
አልቻልኩም እኔ እስካይሽ ባይኔ
ፍቅሬ ያለሽበት አገር አማን ነው
ዎይ አገር አማን ነው
ዎይ አንቺስ ሰላም ነሽ ዎይ
ሰሞኑን አማን ነሽ ዎይ አገር አማን ነው ዎይ
ይጨንቀኛል ዝም ብሎ ይጨንቀኛል
አልቻልኩም እኔ
እስካይሽ ባይኔ
ትዝታዬን ሁሉ ብስለው ብፅፈው
አልቻልኩም ጭንቀቴን መናፈቄን አልተው
እንቅልፍም አላሻኝ ተኛም አላለኝ
እንዳላርፍ አይደል ዎይ ከሀሳብ የጣለኝ
አልጋዬን አንጥፌ እንዴት ልደርበት
አንሶላው ትራሱ ያንቺ ሀሳብ አለበት
ጎኔን ከመኝታ ከኩታው ባገናኝ
ገላዬ ብደርብ ውስጤ መች አስተኛኝ
መች እችላለሁ እኔ ልደብቀው ጉዳቴን
ጭንቅ እያለኝ እኔ እኖራለው ምኞቴን
ሰነበተ መንፈሰ ናፍቆት ሲበትነው
ወገን ዘመድ ጎረቤት ሀገሩስ እንዴት ነው
ሰነበተ መንፈሴ ናፍቆት ሲበትነው
ወገን ዘመድ ጎረቤት ሀገሩስ እንዴት ነው
እቴ ያለሽበት አገር አማን ነው ዎይ
አገር አማን ነው ዎይ
አንቺስ ናፍቀሻል ዎይ ሰሞኑን አማን ነሽ ዎይ
አገር አማን ነው ዎይ
ይጨንቀኛል ዝም ብሎ ይጨንቀኛል
አልቻልኩም እኔ እስካይሽ ባይኔ
ፍቅሬ ያለሽበት አገር አማን ነው ዎይ
አገር አማን ነው ዎይ አንቺስ ናፍቀሻል ዎይ
ሰሞኑን አማን ነሽ ዎይ አገር አማን ነው ዎይ ይጨንቀኛል ዝም ብሎ ይጨንቀኛል
አልቻልኩም እኔ እስካይሽ ባይኔ
የሚያየው ነገር ላይ እየሳለሽ አይኔ
ልረሳሽ አልቻልኩም ተጎዳሁኝ
እኔ እድሌ ሆነና መናፈቅ አይለቀኝ
መሬቱ እንደሰማይ ይውላል ሲርቀኝ
ወዳንቺ ያለውን ወደኔ ስስበው
እንደው ምንም የለ ዞሬ ማላስበው
ማን ያምጣልኝ ወሬ አንቺን ተመልክቶ
ፀጋ ሰውነቴ አማን ነሽ ወይ ከቶ
መች እችላለሁ እኔ ልደብቀው ጉዳቴን
ጭንቅ እያለኝ እኔ እኖራለው ምኞቴን
ሰነበተ መንፈሰ ናፍቆት ሲመትነው
ወገን ዘመድ ጎረቤት ሀገሩስ እንዴት ነው
ሰነበተ መንፈሰ ናፍቆት ሲመትነው
ወገን ዘመድ ጎረቤት ሀገሩስ እንዴት ነው