Evangadi
Gossaye Tesfaye
4:31እንደተዳፈነ እንዳልጠፋ እሳቱ ዛሬ ገብቶኛል ያንቺ መንገድ እየቀኑ መውደድ ምልክትሽ ሲሆን ፍቅርን ማሳያሽን ያኔ እንዳላልኩሽ ተይ ሰለቸኝ መቅናትሽ ተመቸኝ የት ገባህ የት ወጣህ ሲል አፍሽ ላመሉ ምን በላህ ምን ጠጣህ የምትዪኝ ሁሉ ለካስ ፍቅር ነው ቅናት ሚመስለው ለካስ መውደድ ነው ክፋት የሌለው ቅናት ጉትጎታሽን ሳልሰማ ካደርኩኝ ይመስለኝ ጀምሯል ያነስኩ የጎደልኩኝ ለካስ ፍቅር ነው ቅናት ሚመስለው ለካስ መውደድ ነው ክፋት የሌለው እንደተዳፈነ እንዳልጠፋ እሳቱ ዛሬ ገብቶኛል ያንቺ መንገድ እየቀኑ መውደድ ምልክትሽ ሲሆን ፍቅርን ማሳያሽን ያኔ እንዳላልኩሽ ተይ ሰለቸኝ መቅናትሽ ተመቸኝ ለክፉም ለደጉም ለዋሾም ላባዩም ፍቺው ይለያያል ልክ እንደ አተያዩ ለካስ ፍቅር ነው ቅናት ሚመስለው ለካስ መውደድ ነው ክፋት የሌለው ሰው አይቀናምና ሆን ብሎ ፈልጎ ወደሽ መቅናትሽን አየሁት በበጎ ለካስ ፍቅር ነው ቅናት ሚመስለው ለካስ መውደድ ነው ክፋት የሌለው(3)