Marmar

Marmar

Madingo Afework

Альбом: Swedlat, Vol. 3
Длительность: 5:19
Год: 2015
Скачать MP3

Текст песни

ክርትት ባለ ውበት በዝምታ
ቀልብን በሚስብ በመጠነ ፍካት
በሰከነ አንደበት ተናግረሺኝ
አንድ ያለኝ ልቤን አስከፈትሽኝ
ፍስስ ባለ ውበት በዝምታ
ቀልብን በሚስብ በመጠነ ፍካት
በሰከነ አንደበት ተናግረሺኝ
አንድ ያለኝ ልቤን አስከፈትሽኝ
ውበትሽን አድንቄ ለመናገር
አጣው ብዙ ቃላት ቢደረደር
ክብርሽን ላወድስ ካሉት መሃል
አነበብኩ ገልጬ ብዙ መፅሐፍ
በሊቅ በጠቢባን ከተሳሉ
አንድም አንቺን የለም የሚመስሉ
ባጣ ከዚ ሁሉ ሚመስልሽ
መልሶ አስደነቀኝ የማማርሽ
ማር ማር ይላል ከንፈርሽ
ስስት ልክ እንደስምሽ
ማር ማር ደሞ አልሺኝና
ቀረው ጣፈጥሺኝና
ማር ማር ይላል ከንፈርሽ
ለስለስ ልክ እንዳመልሽ
ማር ማር ደሞ አልሺኝና
ቀረው ጣፈጥሺኝና
ክርትት ባለ ውበት በዝምታ
ቀልብን በሚስብ በመጠነ ፍካት
በሰከነ አንደበት ተናግረሺኝ
አንድ ያለኝ ልቤን አስከፈትሽኝ
ፍስስ ባለ ውበት በዝምታ
ቀልብን በሚስብ በመጠነ ፍካት
በሰከነ አንደበት ተናግረሺኝ
አንድ ያለኝ ልቤን አስከፈትሽኝ
ከፍጥረታት ሁሉ በምድር ላይ
ለኔ አልተፈጠረም ካንቺም በላይ
ፈጣሪስ በቃሉ ይሁን ካለው
አብልጦሽ የለም ወይ ከፈጠረው
በሊቅ በጠቢባን ከተሳሉ
አንድም አንቺን የለም የሚመስሉ
ባጣ ከዚ ሁሉ ሚመስልሽ
መልሶ አስደነቀኝ የማማርሽ
ማር ማር ይላል ከንፈርሽ
ሰስቼ ልክ ስምሽ
ማር ማር ደሞ አልሺኝና
ቀረው ጣፈጥሺኝና
ማር ማር ይላል ከንፈርሽ
ለስለስ ልክ እንዳመልሽ
ማር ማር ደሞ አልሺኝና
ቀረው ጣፈጥሺኝና