Lefkir Neber

Lefkir Neber

Tewodros Tadesse

Длительность: 6:53
Год: 2021
Скачать MP3

Текст песни

እኔ አይደለሁም ወይ
የተበደልኩት ከፍቶኝ ሳድር
አልችል ሲለኝ ልቤ
ተከታይ ሆኖሽ ወጥቶ ሲኖር
ፍቅርሽን
ልብሽን
ገላዬዋን አጥቶ ሲቀር አንቺን
አንቺን ብሎ ሲቀር

ለፍቅር አንቺ ዘበናዬ
ጣል ጣል አረግሺኝ
አይከብድሽ የኔው ጉዳዬ
አሄሄ ለመውደድ ጊዜም የለሽ ወይ
ለፍቅር ነበረ መቸገሬ
አንቺን አንቺን እያልኩ ስጨነቅ ሳስብ ማደሬ
አሄሄሄ ምነዋ ትላንት ወደሽ ዛሬ

ሰበር ሰካ ስትይ
እህህን ከመንገድ ትተሽው
ሽፍንፍኑን ፍቅሬን
እህህን ንፋስ አስነካሽው

ግቢሽን
ቤትሽን
ገላዬዋ ልየው ሁሉን
ልምጣ አትከልክይኝ
ያለ ልብ ሰውም ሰው አይሆን
ግቢሽን
ቤትሽን
ገላዬዋ ልየው ሁሉን
ልምጣ አትከልክይኝ
ያለ ልብ ሰውም ሰው አይሆን

አሄሄሄ እሱም ሀገር ሆኖ ዘመድዬ
አሄሄሄ ሆዴ አንቺን ባኖረ አሄ
አሄሄሄ ማን አየብኝና
ማን ሰማብኝና ፍቅርሽ ወጥቶ ቀረ
አሄሄሄ ክትክታ ቢሰበር የኔ ቆንጆ
አሄሄሄ አይታሽም በሰው አሄ
አሄሄሄ እንዲያው መቻል ብቻ
አይን የወደደውን ልብ እስኪመልሰው

እኔ አይደለሁም ወይ
የተበደልኩት ከፍቶኝ ሳድር
አልችል ሲለኝ ልቤ
ተከታይ ሆኖሽ ወጥቶ ሲኖር
ፍቅርሽን
ልብሽን
ገላዬዋን አጥቶ ሲቀር አንቺን
አንቺን ብሎ ሲቀር

ግማሽ ጎንህ ነኝ አለሁ ብላ
ሸሸት ሸሸት ብትል ልቤንም ከኔው ነጥላ
አሄሄሄሄ... ተበላ አንጀቴም ተበላ
ጠላቴ አልልሽ ወድጄሽ
ወዳጅ እንዳልልሽ ዘወትር ህመሜ ነሽ
አሄሄሄ... ሁሉንም ሆነሽ ተገኘሽ

አልተሰናዳሁም
እህህን... ልለይሽ አልቻልኩም
ዛሬም ሆነ ትናንት
እህህን... ደህና ሁኚ አላልኩም
ግቢሽን
ቤትሽን
ገላዬዋ ልየው ሁሉን
ልምጣ አትከልክይኝ
ያለ ልብ ሰውም ሰው አይሆን
ግቢሽን
ቤትሽን
ገላዬዋ ልየው ሁሉን
ልምጣ አትከልክይኝ
ያለ ልብ ሰውም ሰው አይሆን

አሄሄሄ መውደድ መች ጠግቤ የኔ ቆንጆ
አሄሄሄ ፍቅርሽ መቼ በቅቶኝ አሄሄ
አሄሄሄ አምሮቴ መች ወጥቶ ገላሽ መች ተረስቶኝ
ገላሽ መች ተረስቶኝ
አሄሄሄ ውርሱ ማሰብ ሆኖ ዘመድዬ
አሄሄሄ የመውደድ መካሻው አሄ
አሄሄሄ ያልወጣለት ፍቅር ፀፀት አይደለም ወይ
እስከመጨረሻው
አሄሄሄ ውርሱ ማሰብ ሆኖ ዘመድዬ
አሄሄሄ የመውደድ መካሻው አሄ
አሄሄሄ ያልወጣለት ፍቅር ፀፀት አይደለም ወይ
እስከመጨረሻው
አሄሄሄ መውደድ መች ጠግቤ የኔ ቆንጆ
አሄሄሄ ፍቅርሽ መቼ በቅቶኝ አሄሄ
አሄሄሄ አምሮቴ መች ወጥቶ ገላሽ መች ተረስቶኝ
ገላሽ መች ተረስቶኝ
አሄሄሄ አምሮቴ መች ወጥቶ ገላሽ መች ተረስቶኝ
ገላሽ መች ተረስቶኝ
አሄሄሄ አምሮቴ መች ወጥቶ ገላሽ መች ተረስቶኝ
ገላሽ መች ተረስቶኝ