Turun Bulle
Nigusuu Taammiraat
6:27ፀሐይ ነይ ውጪ ጨለማን ግለጪ ልቤ ካልጋው ጥሎኝ ሄደ እየባባ በረረብኝ ወደ ደጅ ጠፍቶበት ያ ልጅ ዓይኔ ባሳብ ፈዞ ሆዴ ቢባባ አላገኛው በቃ እንግዲህ ልጁን ከአሁን ወዲህ ያን የፍቅር ግርማ ሲውጠው ጨለማ ሳቄን ስቀማ ለአፍ ልጫወት እንጂ ደስታ ምን ሊበጅ ጠፍቶ ያ ልጅ ልቤ እንደ ወፍ የትም ዞረለት ከአካላቱ ወቶ ቀረለት ይምጣ እስቲ እንዳለ ልቤ በሱ ናፍቆት ዋለለ (ይምጣልኝ) ጣርያ ግድግዳው (ይምጣልኝ) አልጋ ትራሱ (ይምጣልኝ) እያወራልኝ (ይምጣልኝ) ሁሌ ስለሱ (ይምጣልኝ) እንዴትስ ልርሳው (ይምጣልኝ) እንዴት ልዘንጋው (ይምጣልኝ) በክፍሌ ሞልቶ (ይምጣልኝ) ደጄን ስዘጋው ፀሐይ ነይ ውጪ ጨለማን ግለጪ ልቤ ካልጋው ጥሎኝ ሄደ እየባባ በረረብኝ ወደ ደጅ ጠፍቶበት ያ ልጅ ዓይኔ ባሳብ ፈዞ ሆዴ ቢባባ አላገኛው በቃ እንግዲ ልጁን ከአሁን ወዲ የአባይ በረሀ ሲጠማ አይሰጥ ውሀ ልክ እንደ ደሀ ነኝ የእጅ የሚጠማኝ የራሴ ቤት ለማኝ አምላክ በሰማኝ በአባይ ገመገም ውስጥ ተጉዤ መዋተት ነው እንጂ ምን ይዤ ይምጣ እስቲ እንዳለ ልቤ በሱ ናፍቆት ዋለለ (ሲታየኝ) የገንዳ ውሀ (ሲታየኝ) ሞልቶ ይፈሳል (ሲታየኝ) ግን እኮ ሀሳብ ነው (ሲታየኝ) መች ይታፈሳል (ሲታየኝ) ኮቴው ተሰምቶኝ (ሲታየኝ) በሬ ዳርቻ (ሲታየኝ) ከፍቶ ሚገባው (ሲታየኝ) ትዝታ ብቻ ባይ በሃሳብ ባህር ላይ ወደ ታች ወደ ላይ የህልም አታላይ ሌት መቶ በታንኳ በሬን ባያያንኳኳ እስኪ ነጋ እንኳ ትንፋሹ በሌሊት ይመጣል ልዳብስህም ሲሉት ይታጣል ሲመሰል በራሱ ደረቴ ላይ ያድራል ትራሱ (ሲታየኝ) ኮቴው ተሰምቶኝ (ሲታየኝ) በሬ ዳርቻ (ሲታየኝ) ከፍቶ ሚገባው (ሲታየኝ) ትዝታው ብቻ (ሲታየኝ) ያረፈ መስሎኝ (ሲታየኝ) ጋደም እያለ (ሲታየኝ) በትዝታ እንጂ (ሲታየኝ) በአካል የታለ (ሲታየኝ) ጣርያ ግድግዳው (ሲታየኝ) አልጋው ትራሱ (ሲታየኝ) እያወራልኝ (ሲታየኝ) ሁሌ ስለሱ (ሲታየኝ) እንዴትስ ልርሳው (ሲታየኝ) እንዴት ልዘንጋው (ሲታየኝ) በክፍሌ ሞልቶ (ሲታየኝ) ደጄን ስዘጋው ሲታየኝ ሲታየኝ ሲታየኝ ሲታየኝ ሲታየኝ ሲታየኝ ሲታየኝ ሲታየኝ