Zemnanit

Zemnanit

Tsegaye Eshetu

Длительность: 5:34
Год: 2013
Скачать MP3

Текст песни

ቆይ የኔ ዘምናን ዘምናኒት የኔ ዘምናን
በይ የኔ ዘምናን ዘምናኒት የኔ ዘምናን
ለፍቅሯ ማርከሻ ታጣላት መድሃኒት
ታጣላት መድሃኒት

ቆይ የኔ ዘምናን ዘምናኒት የኔ ዘምናን
በይ የኔ ዘምናን ዘመናኒት የኔ ዘመናን
እንደዉ ለሷ መርቻ ታጣላት መድሃኒት
ታጣላት መድሃኒት

ከማር እንካ ብላ ወለላ አሳይታኝ
በጣዕም አስከንፋ በጣዕም አስፈትታኝ
አበደም ብትለኝ አልፈዋለዉ ችዬ
ለማን አማታለዉ ስም አጠፋች ብዬ
ለማን አማታለዉ ስም አጠፋች ብዬ

ዛሬም ዘበናይ ነገም ዘበናይ
ባይሆን አንዳንዴ አትመችም ወይ
መሸም ዘበናይ ነጋም ዘበናይ
ወዳጅ አንዳንዴም አይመችም ወይ

አረ እናንዬ ይሄን ገበናዬን እንዴት ልሸሽገዉ
እንዴት ልሸሽገዉ
ነገር ሆዴ ገብቶ ክፍት እያረገዉ
ክፍት እያረገዉ

አረ ናንዬ ሰዉ ሁሉ ከዉስጡ እየፈላለገዉ
አረ ናንዬ እየፈላለገዉ አረ ናንዬ እንደዉ
የኛ ነገር ዛሬም ሀላል ነዉ ዛሬም ሀላል ነዉ
ዘምናንዬ ወይ ዘምናንዬ
ዘምናንዬ ወይ ዘምናንዬ
ዘምናንዬ ወይ ዘምናንዬ
ዘምናንዬ ወይ ዘምናንዬ

ቆይ የኔ ዘምናን ዘምናኒት የኔ ዘምናን
በይ የኔ ዘምናን ዘምናኒት የኔ ዘምናን
እንደው እሷ መርቻ ታጣላት መድሃኒት
ታጣላት መድሃኒት

ተይ የኔ ዘምናን ዘምናኒት የኔ ዘምናን
በይ የኔ ዘምናን ዘምናኒት የኔ ዘምናን
ለፍቅሯ ማርከሻ ታጣላት መድሃኒት
ታጣላት መድሃኒት

ስታዘዝ መኖሬን ባሻነቴን አይታ
ማፍቀርም ሳይከብዳት ሳይመስላት ዉለታ
አልባስ የቸገረዉ የጐበዝ ደሃ አርጋ
አዲስ ለምዳ መጣች ሰግዳ ልታዋጋ
አዲስ ወዳ መጣች ወስዳ ልታዋጋ

ዛሬም ዘበናይ ነገም ዘበናይ
ባይሆን አንዳንዴ አትመችም ወይ
መሸም ዘበናይ ነጋም ዘበናይ
ወዳጅ አንዳንዴም አይመችም ወይ

አረ እናንዬ የአምሳሉ ተመሳይ የአምላክ ልጅ አዳሙ
የአምላክ ልጅ አዳሙ
የሩቅ ይታየዋል እንኳን የገዳሙ እንኳን የገዳሙ

አረ እናንዬ የት ገባሽ የት ወጣሽ
አረ እናንዬ የት ቆየሽ ባልልም
አረ እናንዬ የት ቆየሽ ባልልም
አረ እናንዬ ሆድ ሆዴን ያልበላኝ
አረ እናንዬ ያልቆጨኝ መሰል
አረ እናንዬ ያልቆጨኝ መሰል
ዘምናንዬ ወይ ዘምናንዬ
ዘምናንዬ ወይ ዘምናንዬ
ዘምናንዬ ወይ ዘምናንዬ
ዘምናንዬ ወይ ዘምናንዬ