Ewenetuen Negeregne
Tsedenia G
5:24አቤት ያቺን እለት አቤት ያቺን ማታ ልጅነቴን ላንተ የሰጠሁኝ ለታ በፍርሀት በሀፍረት በስጋት በጉጉት ጭንቀት በሚያርደው በልጅነት ስሜት መቼም የማረሳው የእድሜ ትውስታዬ የልጅነት ጌጤ ብራምባር አልቦዬ በስጋ በመንፈስ በሀሳብ በስሜት በአንድ ልብ ዜማ በአንድ ትንፋሽ ቅኝት የሰራ አካላቴ በአንድ ስልት ሰምሮ በአንድ ላይ ጨፈረ ከ'ካልህ ጋር አብሮ አቤት ያቺን እለት አቤት ያቺን ማታ ልጅነቴን ላንተ የሰጠሁኝ ለታ አካሌ በአካልህ ፍቅርን ተማረ የሴትነት ወጉን 'ሀ' ብሎ ቆጠረ አቤት ያቺን እለት አቤት ያቺን ማታ ልጅነቴን ላንተ የሰጠሁኝ ለታ አዲስ አለም አየሁ አየሁ አዲስ ሂወት በአንድ ቀን አገኘው ፍቅርና ሴትነት እንዲ አዲስ እውነት ባንዴ እንዳሳወቀኝ አምላክ አደራውን በአንድ እምነት ያዝልቀው ምድር ሙሉ ፍቅር ሰማይ ሙሉ ደስታ ቀዳሁ ከትንፋሽ ባህር ሙሉ እርካታ ያቺን ቅስበት ህልሜ የአንድ አፍታ ሰመመን አልፋና ኦሜጋ እውን ትሁን አሜን አቤት ያቺን እለት አቤት ያቺን ማታ ልጅነቴን ላንተ የሰጠሁኝ ለታ አካሌ በአካልህ ፍቅርን ተማረ የሴትነት ወጉን 'ሀ' ብሎ ቆጠረ አቤት ያቺን እለት አቤት ያቺን ማታ ልጅነቴን ላንተ የሰጠሁኝ ለታ አይህ... አይህ... አይህ... አይህ... አይይይ አይይይ አይይይ አይይይ አይይይ አይይይ አይይይ አይይይ