Bementa Gemedew

Bementa Gemedew

Tsedenia Gebremarkos

Альбом: Yefikir Girma
Длительность: 5:24
Год: 2016
Скачать MP3

Текст песни

ገና ሳንፈጠን ያወቀን ለይቶ
በፍቅር ያኖረን በትዳር አፅንቶ
ሁሉ ማያልቅበት መስጠት የሚወደዉ
ትስስራችንን በመንታ ገመደዉ
ገና ሳንፈጠን ያወቀን ለይቶ
በፍቅር ያኖረን በትዳር አፅንቶ
ሁሉ ማያልቅበት መስጠት የሚወደዉ
ትስስራችንን በመንታ ገመደዉ
ለታመነዉ ፍቅር ላከበረዉ ገላ
ለሞቀዉ ቤታችን ሀሴት ሰስናሰላ
ባልነትህ ጥሞኝ ህይወቴ ሲፈካ
በኔ ስትኮራ አይቶን ነበር ለካ
ለታመነዉ ፍቅር ላከበረዉ ገላ
ለሞቀዉ ቤታችን ሐሴት ሰስናሰላ
ባልነትህ ጥሞኝ ህይወቴ ሲፈካ
በኔ ስትኮራ አይቶን ነበር ለካ
ማብላት ማጠጣቱ ማስጌጡ መኳሉ
ትምህርት ቤት መላክ ማዝናናትን ቢሉ
ቀላል ናቸዉና እኔዉ ምችላቸዉ
ወንድነትን እስቲ አንተ አስተምራቸዉ
ለእነሱ የሚሆን ለኔ ያልታደለ
ሁሌ ማደንቅልህ አንተጋ ስላለ
ዉድ ልጆቻችን ሁሉ እንያምርላቸዉ
ወንድነትን ብቻ አንተ አስተምራቸዉ
ትላንትን ስለኛ ነገን ስለነሱ
አጣምረዉ ሊያሳዩን ወስደዉ ሚመልሱ
ከመልክህ ከመልኬ ነጣጥሎ ኮርጆ
ልጅ መስታወት ሰጠን ያዉም ሁለት ቆንጆ
ትላንትን ስለኛ ነገን ስለነሱ
አጣምረዉ ሊያሳዩን ወስደዉ ሚመልሱ
ከመልክህ ከመልኬ ነጣጥሎ ኮርጆ
ልጅ መስታወት ሰጠን ያዉም ሁለት ቆንጆ
እሹሩሩ ፍቅሩ ፍቅር እሹረሩሩ
አናንተንም የሰጠን ይክረምልን አዉ
እሹሩሩ ፍቅሩ ፍቅር እሹረሩሩ
አናንተንም የሰጠን ይክረምልን አዉ
እሹሩሩ ፍቅሩ ፍቅር እሹረሩሩ
አናንተንም የሰጠን ይክረምልን አዉ